በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ተጀምረው የነበሩ በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን የክልሉ  የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገለፀ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ተጀምረው የነበሩ በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን የክልሉ  የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገለፀ

ሀዋሳ፡ የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ተጀምረው የነበሩ በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን የክልሉ የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው ባለፉት ሰድስት ወራት በውሃ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ  ገምግሟል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደገለፁት፤ ያለፉት ወራት አፈፃፀም ክልሉ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ከቢሮ ማደራጀት ጀምሮ በርካታ ስራዎች ተሠርቷል።

በክልሉ ከዚህ በፊት በነባሩ ክልል ተጀምረው ያልተጠናቀቁ በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች ነበሩ ያሉት ኃላፊው አሁን ላይ ፕሮጀክቶቹ እየተገባደዱ ነው ብለዋል።

የውል ጊዜያቸው በመጠናቀቁ በሚቀጥለው አመት የአግልግሎት ጊዜያቸውን ለመጨረስ የተቃረቡ ፕሮጀክቶች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫች ናቸው ብለዋል አቶ ዳዊት።

በዕቅድ አፈፃፀሙ ላይ የተገኙ የቢሮው ሰራተኞች ቢሮው ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በውሃ ዘርፍ አመርቂ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ለአብነትም ከዚህ በፊት በህዝብ ዘንድ በየጊዜው ጥያቄ ይነሳባቸው የነበሩ እንደ የወልቂጤ ከተማ የውሃ አገልግሎት ለውጥ የታየባቸው ናቸው ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የውሃ ዘርፍ የ6 ወር አፈፃፀም የነበሩ ጠንካራ ስራወችን ማስቀጠል የሚቻልባቸውንና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫወችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ አሰፋ ፀጋዬ – ከወልቂጤ ጣቢያችን