የኢንተር ሚያሚን ማለያ ለብሶ ፎቶ በመነሳቱ የኢንተርሚያምን ጨዋታ እንዳይመራ የተከለከሉ ዳኛ
ከሰሞኑ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በአሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ኢንተር ሚያሚ ከኦርላንዶ ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ መርሐግብሩን እንዲመሩ የተመረጡት ዋና ዳኞች መነጋገሪያ ሆነዋል።
የፕሮፌሽናል ዳኞች ማህበር በቅድሚያ ጉይሄርሜ ሴሬታ የተሰኙ ዳኛ ለዚሁ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመድባቸዋል።
ግን ጨዋታው ሊጀመር ሰዓታት ሲቀሩት በጄሚ ሄሬራ ይቀየራሉ።
መጀመሪያ የተመደቡት የጨዋታ ዳኛ የተቀየሩበት ምክንያት የኢንተርሚያምን ማሊያ ለብሰው የተነሱት ፎቶ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ሲዘዋወር በመታየቱ ነው።
በዕለቱ አራተኛ ዳኛ በመሆን ተመድበው የነበሩት ጄሚ ሄሬራ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንደሚሩት እና በእሳቸው ምትክ ኢቫን ሲድ ክሩዝ እንደመሩት ተደረገ።
ጨዋታውን ኢንተርሚያሚ ሉይዝ ሱዋሬዝ እና ሊዮኔል ሜሲ እያንዳንዳቸው ሁለት ጎል እንዲሁም ቴይለር አንድ ግብ በማከል ጨዋታውን 5ለዐ በሆነ ውጤት አሸንፎ መውጣቱ ይታወቃል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው