ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በስልጢ ሀይቅ ዙሪያ የለማ የሙዝ ማሳ እየጎበኙ ነው
ሀዋሳ: የካቲት 28/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው የተመራ የክልሉ አመራር በስልጤ ዞን ምስራቅ ስልጢ ወረዳ ስልጢ ሀይቅ ዙሪያ የለማ ሙዝ ተመልክቷል::
በስልጢ ወረዳ የ30 40 30 ፕሮጀክት በ2014 ዓ.ም የተጀመሩ የተለያዩ ፍራፍሬዎች በክላስተር ለምተዋል::
በስልጢ ሀይቅ ዳርቻ ቀደም ሲል ባህር ዛፍ ተተክሎ የነበረ ሲሆን ባህር ዛፎችን በማንሳት ነው ከአንድ አመት በፊት በሙዝ ምርት የተተካው::
ባህር ዛፍን በሙዝ መተካት ያስፈለገበት ምክንያት ከሚኖረው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር መሆኑን ለክልሉ አመራር ገለፃ ያደረጉት የምስራቅ ስልጢ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሳሎ ፋኒ ተናግረዋል::
25 ሄክታር መሬት ላይ ከለማው የሙዝ ምርት በተጨማሪ በ105 ሄክታር መሬት ላይ በአካባቢው ከለሙ ሌሎችም ፍራፍሬዎችም አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል ብለዋል::
በስልጢ ሀይቅ ዳርቻ የለማው ሙዝ የአይቻልምን አመለካከት የሚቀይር ነው ያሉት ደግሞ የስጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ናቸው::
በምስራቅ ስልጢ ወረዳ የታየውን ውጤታማ የሙዝ ልማት ሥራን በዞኑ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎችም ልምድ የማስፋት ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል::
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አካባቢው ላይ የታየው የሙዝ ልማት አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል::
በተጀመረው ትጋት በመቀጠል በሁሉም የልማት መስክ በክልሉ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መስራት ይኖርብናል ብለዋል::
በመስክ ምልከታው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ: ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር: በምክል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በመስክ ምልከታው ተሳትፈዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ በ72 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ከኮይቤ ማቃና የ12 ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የመንግድ ግንባታ ስራ ተጀመረ
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ29 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል