የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከዱቄት ፋብሪካ ባለቤቶች ጋር የዉይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ የዱቄት ፋብሪካ ባለቤቶች ጋር የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በመፍትሔዎች ዙሪያ የዉይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ እንዳሉት፤ ክልሉ በዲስ መልክ ከተደራጀ ወዲህ በርካታ ስራዎችን ሲተገብርና ሲያከናዉን ቆይቷል።
በንግዱ ዘርፍ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ ባለቤት ሆነው እንዲገለገል ለማድረግ በተሰራ ስራ የኦን ላይን አገልግሎት መስጠት ተችሏል።
መሰረታዊ የንግድ ስርዓት ማዘመን ዋነኛ መሆኑን በመግለፅ ስርዓቱ እንዳይዘምን የሚያደርጉ ማነቆዎችን መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ስልጤ ዞን ላይ 50 የሚሆኑ የዱቄት ፋብሪካዎች እንዳሉ በማንሳት አሁን ላይ 30 የሚሆኑት ብቻ ስራ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
አክለውም ሁሉም ፋብሪካዎች በስራ ላይ እንዲዉሉና በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት መፍትሄ በመስጠት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ቢሮው እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስሀቅ ማሶሬ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የዞንና ልዩ ወረዳ የንግድና ገበያ ልማት ተቋማት ኃላፊዎችና የዱቄት ፋብሪካ ባለቤቶች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘዉዱ
More Stories
በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ ተደረገ
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ