ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ሀላባ ዞን ገብተዋል

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ሀላባ ዞን ገብተዋል

ሀዋሳ: የካቲት 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የተመራ የክልሉ አመራር ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ገብቷል:

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራር ቡድን በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንብጣ ቀበሌ የመስኖ ልማት ሥራዎችን ተመልክቷል::

በቀበሌው በሶላር ሀይል በመታገዝ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ አቡካዶ፣ ፓፓዬና ሌሎችም የጓሮ አትክልቶች ለምተዋል::

በመስክ ምልከታው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ በምክል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በመስክ ምልከታው ተሳትፈዋል::

ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ