በልማት ላይ በአርበኝነት መሥራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
ሀዋሳ: የካቲት 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የተመራ የክልሉ አመራር በከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ የግብርና ኢንቨስትመንት ልማት ሥራን ተመልክቷል::
በወረዳው በ10 ሄክታር መሬት ላይ በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የለማውን የበጋ መስኖ ስንዴና የጓሮ አትክልት የተመለከቱት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው አበረታች ሥራ ማየታቸውን ገልጸዋል::
በማሳው የታየውን መልካም ተሞክሮ በአቅራቢያ ባሉ አርሶ አደሮች እና በሌሎችም አካባቢዎች ማስፋት እንደሚገባ አንስተዋል::
አባቶቻችን በአርበኝነት ሀገርን ጠብቀው አስተላልፈውልናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እኛም በግብርና፣ በጤና በትምህርትና በሌሎችም መስኮች ለትውልድ የሚበቃ የአርበኝነት ሥራ መፈፀም ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል::
ርዕሰ መስተዳድሩ የመስክ ምልከታው ዋና ዓላማ የግብርና እና የኢንቨስትመንት ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ እንዲሁም ጥንካሬዎችን እና ጉድለቶችን በመስክ ላይ ለማየትና ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል::
በከምባታ ዞን ተዘዋውረው የተመለከቷቸው በኢንዱስትሪው እና በግብርናው ረገድ የተከናወኑ ተግባራትም ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በመስክ ምልከታው ተሳትፈዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
“ትንንሽ የሚመስሉ ስራዎች ለትልልቅ ዕድሎች በር ይከፍታሉ” – ወይዘሮ ህልውና ጌታቸው
የህግ ታራሚዎችን በስነ ምግባር ለማነፅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለፀ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች በክህሎት የበቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ጥራት ያለውን ስልጠና መስጠታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠቀ