የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተወካዮች መረጣ እና የአጀንዳ አሰባሰብ ሂደቱን አጠናክሮ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዞኖች አጀንዳ የሚሰጡ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ምርጫን በተመለከተ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ውስጥ ካሉ 11 ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚቀርቡትን አጀንዳዎች በማሰባሰብ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ ተወካዮች መረጣ ከየካቲት 26 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም 6ኛ ድረስ ይካሄዳል ብለዋል።
በተወካዮች መረጣው ላይ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ወጣቶች፣የንግዱ ማህበረሰብ ፣መምህራን፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
የተወካይ መረጣ እና የአጀንዳ አሰባሰብ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን የዞኑ ህዝብ እና ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:-ሲሳይ አፃ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ