የአከባቢ ሰላምን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ሚና ትልቅ ቦታ አለው – አቶ ተስፋዬ ይገዙ
ሀዋሳ፡ የካቲት 25/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት አባላት በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በህዝብ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ።
የህዝብ ተወካዮቹ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመንግሥት አካላት አቅርበዋል ። የሚመለከታቸው አካላትም መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በዚህ ወቅት እንደገለፁ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ግዴታውን ሊወጣ የገባል ብለዋል።
በክልሉ መሠረታዊ የመዋቅር ጥያቄዎች የተመለሱ በመሆኑ ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ልማት ብቻ እንዲያዞር ጥሪ አቅርበዋል ።
በክልሉ በርካታ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ወጪ ግንባታ ላይ ናቸው ያሉት አቶ ተስፋዬ፥ መንግስት የጀመራቸውን መጨረስ እንጂ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር ዕቅድ የለውም ብለዋል።
ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ ግብርና የማምረቻው ዘርፍና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች የክልሉ ምጣኔ ሀብት መሠረት ለማድረግ ልዩ ዕቅድ መያዙንም ጠቁመዋል ።
በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠርና የተላላፊ በሽታዎችን ስጋት ለመግታት በትኩረት የክልሉ መንግስት እንደሚሰራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል ።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ