ሁሉም ቤተ-እምነቶች ለሠላምና አንድነት ከመንግስት ጎን በመቆም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
በአሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የጂንካ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስረታ በተካሄደበት ወቅት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሬ እንደገለፁት ሙስሊሙ ማህብረሰብ ከመንግስት ጎን በመቆም ለሠላም የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሪ ዞንና ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ማታዶ በርቢ እና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ አበራ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ሠላምና አንድነት ከሁሉም ልማት የሚቀድም ተግባር በመሆኑ ሁሉም ቤተ-እምነቶች በዚህ ልክ ጠንክረው ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የተመሰረተው የጂንካ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሠላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የበኩሉን የማይተካ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የመንግስት የሥራ ሀላፊዎቹ አሳስበዋል።
የአሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጀማል መሐመድ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚመሰረቱ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች ለሠላም ጠንክረው እንደሚሰሩ ገልፀው ማንኛውም የውስጥ ችግር ካለ በእነዚህ መዋቅሮች በንግግር የሚፈታ ይሆናል ብለዋል።
በምስረታው በጂንካ ከተማ አስተዳደር የሚሠሩ አካላት የተሰየሙ ሲሆን የተመረጡ አባላትም ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ወይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል
ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከዞን እስከ ወረዳ የህዝቡን አስተያየት መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበት በጀት አመት ነበር ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ