ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍፃሜ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
በግላስኮው እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ የሚካፈሉበት የ3ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።
የሴቶች 3ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ምሽት 5፡15 ላይ ሲጀምር ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋዬ፥ ሂሩት መሸሻ እና ለምለም ሃይሉ የምትወከል ይሆናል።
በሻምፒዮናው በ3ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ካለፉት 10 የወርቅ ሜዳሊያዎች ዘጠኙን ያሸነፉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው።
የወቅቱ የርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ለምለም ሃይሉ አሸናፊነቷን ለማስጠበቅ ትወዳደራለች።
ምሽት 5፡40 ላይ በሚጀምረው የ3ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ጌትነት ዋለ ኢትዮጵያን በመወከል ይወዳደራሉ።
ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተጨማሪ ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በአሜሪካ የተወለደው ያሬድ ንጉሴ እና ስኮትላንዳዊው ጆሽ ኬር ሌሎች ተፎካካሪ አትሌቶች ናቸው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው