128ኛው የአድዋ ድል በዓል በቤንች ሸኮ ዞን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
“ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል “በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው በዓል ላይ የክልል፣ ዞን ፣ የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም የተለያዩ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ አድዋን የሚዘክር ፅሁፍ ያቀረቡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የስነ -ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ እንደተናገሩት አድዋ የኢትዮጵያውያን ድል፣ የአፍሪካውያን ኩራትና የመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ መሆኑን ትውልዱ መገንዘብ ይገባዋል ብለዋል።
አድዋ ጀግኖች አባቶች በሰሩት ታላቅ ገድል በአለም አደባባይ ከፍ ብለን እንድንታይ ያደረገ ታላቅ ገድል መሆኑን ገልጸዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ እና የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ መኩሪያ በበኩላቸው አድዋ ሲዘከር ለትውልዱ የሚያስተላልፈው ትምህርት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ በበኩላቸው የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር አሁን ያለው ትውልድ በልማቱና በሠላሙ በኩል እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ምን ያህል ነው ብሎ እራሱን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ዛሬ ያለው ትውልድ አድዋን ሲያከብር አሁን ላይ የሚታዩ ሀገራዊ አንድነታችንን የሚሸረሽሩና ልዩነትን የሚያሰፉ ሀሳቦችን ለመፍታት በሚያስችል መልኩ መስራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ ፡ ጦያር ይማም- ከሚዛን ቅርንጫፍ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ