የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በወላይታ ዞን ለተከታታይ 4 ቀናት ስያካሂድ የቆየው ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የሚሰጡ የማህበረሰብ ተወካዮች መረጣ ተጠናቀቀ
ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በወላይታ ዞን ለተከታታይ 4 ቀናት ስያካሂድ የቆየው ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የሚሰጡ የማህበረሰብ ተወካዮች መረጣ ተጠናቋል።
በዞኑ የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ አጀንዳ የሚሰጡ ተወካዮች መረጣ ፍፁም ፍታሀዊነት በተሞላ መልክ መከናወኑን ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
ምክክር ኮሚሽኑ የማንም ጣልቃ ገብነት ሳይኖር በሀገራዊ ጉዳይ የዜጎች እኩል ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የጀመራቸው ሥራዎች ይበል የሚያሰኝ ነው ሲሉም አክለዋል።
የውክልና ምርጫ አፈጻጸም ሂደቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳተፈ መሆኑ በእጅጉ እንዳስደሰታቸው አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
የተወከሉ አካላትም ትክክለኛ የህዝብ ጥያቄዎችን ለይቶ አጀንዳ በመስጠት የህዝቡን ውግንና ማሳየት አለባቸው ሲሉም አክለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው የሀሳብ ልዩነቶች ወደ ግጭት መምራት የለባቸውም በማለት በንግግርና ምክክር ጠቃሚ ሀሳቦች በማፍለቅ ሀገርን በጋራ መገንባት እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በቀጣይም በሀገር ደረጃ በሚደረጉ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እውነትን መሰረት ያደረገ የህዝቦች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።
ግልጽ የሆነ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ በህዝቦች መካከል የመተማመንና ተቀራርቦ የመስራት ባህልን ለማጎልበትም ብሎ አብሮ ለማደግም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው በአጽንዖት ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ