ዓድዋ ድል ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል 128ኛው የአድዋ ድል በዓል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተከበረ

ዓድዋ ድል ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል 128ኛው የአድዋ ድል በዓል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተከበረ

ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዓድዋ ድል ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል 128ኛው የአድዋ ድል በዓል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተከብሯል።

የፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ዶክተር ጉቼ ጉሌ እንዳሉት፤ በዓሉ በሀገሪቱ የሚፈጠሩ አንዳንድ የሀሳብ ልዩነቶችን በጋራ ለመፍታት የጋራ ምክክር የምናደርግበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

አድዋ የመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና በትብብር ድል የተቀዳጀንበት ቀን መሆኑንም አንስተዋል።

እኛ ስንተባበር ጠላቶቻችን ማሳፈር እንችላለን ያሉት ፕሬዝደንቱ ሀገርን ለማሻገር የጋራ ትብብር እና አንድነት ከምንም ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ጉዳይ ነው ሲሉም አክለዋል።

በፓናል ውይይቱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ጉቼ ጉሌ፣ የዩኒቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን