በፕሪሚዬርሊጉ ሀድያ ሆሳዕና መቻልን አሸነፈ
ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬርሊግ ሃድያ ሆሳዕና መቻልን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሃድያ ሆሳዕና የማሸነፊያ ግቦችን መለሰ ሚሻሞ፥ግሩም ሃጎስ (በራሱ ላይ) እና ተመስገን ብርሃኑ አስቆጥረዋል።
ለመቻል አቤል ነጋሽ እና ከነዓን ማርክነህ ከሽንፈት መታደግ ያልቻሉ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሀዋሳ ይጫወታሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል
ስፖርት የወንድማማችነት እና የልማት መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ