በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ዞን የጂንካ ከተማ ም/ቤት የ2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ዞን የጂንካ ከተማ ም/ቤት የ2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡
በጉባኤዉ የምክር ቤት አባላት፣ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የማናጅመንት አባላት፣ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ጉባኤዉ የተጀመረዉ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር በመሆኑ የዘንድሮዉን ጉባኤ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል አባላቱ፡፡
በጉባኤዉ የ2015 ዓ.ም 2ኛ ዙር 7ኛዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃሌ ጉባኤ፣ የ2015 ዓ.ም 2ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ቃለ ጉባኤ፣ የምክር ቤቱ የ2016 ዓ.ም ዕቅድ፣ የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፣ ሹመት እና ለሎች አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ የተለያዩ የማስተካከያ ሐሳብና አስተያየት አንስተው አጀንዳዎቹን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡
በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የግለሰቦች የፓርቲ ቁመናን፣ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ተነሳሽነት ታሳቢ በማድረግ የካቢኔ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ወ/ሮ አበራሽ አበበ የጂንካ ከተማ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
ተሿሚዎች በቁርጠኝነት፣ በተነሳሽነት፣ በታማኝነት እንዲሁም ዉጤት ለማምጣት ጠንክረዉ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ገልፀዋል፡፡
ቀደም ሲል የተለያየ አፈፃፀም “ክፍተት መኖሩን አንስተዉ በቀጣይ ያላቸዉን ሀላፊነት እና ዕዉቀት ተጠቅመዉ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የህዝቡን ተጠቃምነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተዉ የሚሰሩ መሆናቸዉን አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ መላኩ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠሩ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚናን በተመለከተ የጋራ ውይይት በጂንካ ከተማ ተካሄደ
ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ