የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ያላቸውን ትልቅ ፍቅርና አንድነትን የሚያሳይ ታሪካዊ ዕሴት ነው- ምሁራን

የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ያላቸውን ትልቅ ፍቅርና አንድነትን የሚያሳይ ታሪካዊ ዕሴት ነው- ምሁራን

ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ያላቸውን ትልቅ ፍቅርና አንድነትን የሚያሳይ ታሪካዊ ዕሴት መሆኑን በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኙ ምሁራን ተናገሩ፡፡

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል የታሪክ ምሁሩ አቶ አሰፋ ገብረ ማሪያም፣ በቦንጋ ትምህርት ኮሌጂ የጂኦግራፍ መምህርና የማህበራዊ ሳይንስ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬከትር መምህር አስረስ አዛዥና የጂኦግራፍ መምህርና የአካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር አልማው ብሩ የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዊያን ጥቁር ሕዝቦች ትልቅ የድል በዓል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

አውሮፓዊያን በጥቁር ሕዝቦች አይሸነፉም የሚለውን ብቻ ሳይሆን ጥቁሮችም አውሮፓዊያንን አያሸንፉም የሚለውን አመለካከትና አስተሳሰብን መቀየር የቻለ የድል ብስራት ነው ብለዋል አስተያየት ሰጪዎች ።

ኢትዮጵያዊያን በማሸነፋቸው ለአፍሪካዊያንና ለአለም ጥቁር ሕዝቦች ትልቅ የታሪክ ቅርስና አውሮፓዊያን ደግሞ ራሳቸውን እንዲፈትሹ ያደረገ ድል ነው ብለዋል ፡፡

በአድዋ ጦርነት ውስጥም የሴቶች ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ሚናቸውን መወጣታቸውን አስታውሰዋል ፡፡

የአድዋ ድል በዓልን ተከትሎ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ አክለዋል፡፡ይሁን እንጂ መንግስታት ሲቀያየሩ የተለያዩ ክፍተቶች መታየታቸውን ጠቁመዋል ፡፡

የዘንደሮውን የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና አንድነትን ያሳየ ትልቅ እሴት መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የአሁኑ ትውልድም የአባቶችን አርአያነት በመከተል ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕውቀትና ክህሎት በመጨበጥ ሀገራችንን ከድህነትና ለማውጣት ሊተጋ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡ መለሰ ገብሬ- ከቦንጋ ቅርንጫፍ