128ኛው የአድዋ የድል በዓል በዲላ ከተማ ተከበረ
ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) 128ኛው የአድዋ የድል በዓል በዲላ ከተማ ተከብሯል።
በበዓሉ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ ወጣቱ ትውልድ ከአድዋ ድል ትምህርት በመውሰድ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቁርጠኛ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።
የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በበኩላቸው አድዋ የብሔራዊ ክብር ማህተም የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል መሆኑን ጠቅሰው ለድሉ ምላሽ መስጠት የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
በዓሉ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
ዘጋቢ : አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ወደስራ ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ
በፍየልና በግ ማሞከት ተግባራት ላይ በመሰማራታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን በሀዲያ ዞን አንዳንድ የሶሮ ወረዳ ሴቶች ተናገሩ
የገጠር ተደራሽ መንገድ የበርካቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እየፈታ መሆኑ ተገለጸ