የስደተኞች ጀልባ ሰጥማ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ
ሀዋሳ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወደ አውሮፓ ለመሻገር ጉዞ የጀመሩ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በሴኔጋል ሰሜናዊ ክፍል በሚገኝ ባህር ውስጥ ሰጥማ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አፍሪካዊያን ስደተኞች ጀልባዋን ተሳፍረው ጉዞ ከጀመሩ ሳምንት እንዳለፋቸው ተገልጿል፡፡
ስደተኞቹ በሴኔጋል ባህር ከሰጠሙ በኋላ በባህሩ ላይ የ20 ሰዎች አስከረን ተገኝቷል ብለዋል የሀገሪቱ ባለሥልጣናት፡፡
የህይወት አድን ሠራተኞች የ20 ሰዎችን ሕይወት ማዳን መቻላቸውም ነው የተገለፁት ፡፡
ጀልባዋ ሴኔጋልን ለቃ ስትወጣ ከ200 እስከ 300 የሚጠጉ ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ጉዞ የጀመረችው፡፡
የሴኔጋል ባህር ዳርቻ ስፔን ደሴት ደርሰው ወደ አውሮፓ ለሚሻገሩ አፍሪካዊያን ስደተኖች ሁነኛ ስፍራ ነው ሲል ቲአርቲ ዘግቧ፡፡
አዘጋጅ፡ መስከረም አበበ
More Stories
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ