“በታንዛኒያ የሀዘን ጊዜ ደማቅ በሆነ አቀባበል በሀገራቸው የተቀበሉኝን ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህን አመሰግናለሁ”- ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በታንዛኒያ የሀዘን ጊዜ ደማቅ በሆነ አቀባበል በሀገራቸው የተቀበሉኝን ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህን አመሰግናለሁ ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀድሞ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት አሊ ሀሰን ሙዊኒይ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገልጸዋል፡፡
“የዛሬው የሁለትዮሽ ውይይት ለዛሬው ጠንካራ ግንኙነታችን መንገድ የከፈተውን ታሪካዊ ትስስራችንን ያመላከተ ነበር። ዛሬ በግብርና፣ በኃይል ንግድ እና በባህል ትብብር የተፈራረምናቸው የመግባቢያ ሰነዶች ለቀጠለው እና ተናባቢ ለሆነው የልማት ስራችን መሰረት ናቸው።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል፡፡
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ