የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጡ 5 የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር አዋጆችና ደንቦችን ተቀብሎ አጸደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጡ 5 የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር አዋጆችና ደንቦችን ተቀብሎ አጸደቀ

ሀዋሳ፡ የካቲት 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ያለውን የገቢ አሰባሰብና አስተዳደር፥ ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር የክልሉ ህገ-መንግስት በሚሰጠው ስልጣን መነሻ፥ የገቢ አቅሙን ለማጠናከር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ለማበጀት በተሠራው ስራ 5 አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

1 የገቢ ግብር አዋጅ፣

2 ተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣

3 የታክስ አስተዳደር አዋጅ፣

4 የቴንብር ቀረጥ አዋጅ እና

5 የከተሞች አስተዳደር አዋጅ፣

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ፥ የቀረበለትን የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር 5 ረቂቅ አዋጆችን ገንቢና ጠቃሚ የማስተካከያ አስተያየቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ሲያፀድቅ የከተሞች አስተዳደር አዋጅ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ አጽድቋል።

ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ