የዓለም አቀፉ የፍልሰትድርጅት( IOM)ኢትዮጵያመደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን፣ የተመላሽ ዜጎችን ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ጋር በተያያዘ ለምትሠራውን ስራ እገዛ ማድረጉን አስታወቀ
ሀዋሳ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት( IOM) ሪጅናል ዳይሬክተር ራና ጃበር እና በኢትዩጵያ ቺፍ ኦፍ ሚሽን ከሆኑት አቢባቱ ዋኔጋር ተወያይቷል።
በዉይይቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን በመከላከል፣ የተመላሽ ዜጎችን ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከነዚህም ተግባራት መካከል መደበኛ ባልሆነ መልኩ ለስደት የተጋለጡ ዜጎችን ወደ አገራቸው መመለስና ወደ ቤተሰቦቻቸውና ወደ መጡበት አካባቢ የመመለስ ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሚኒስትሯ አክለውም መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ከምንጩ መካላከል ላይ ያተኮሩ ስራዎች እና ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ምቹ ሀገር እንድትሆን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
ተመላሽ ዜጎች በተለይም ወላጆቻቸውን በስደት ላጡ ህፃናት፣ ሴቶች ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው መልሰው ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ እና ዘላቂ የሆኑ የመጠለያ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ማስፋፋት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አሳስበዋል።
በተጨማሪም ሚኒስትሯ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በኢትዮጵያና በዜጎቿ ላይ እያስከተለ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ ለመቀነስ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት( IOM) ካሉ ተቋማት ጋርም በትብብርና በቅንጅት መስራቱንም እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የየዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት( IOM)ሪጅናል ዳይሬክተር ራና ጃበር በበኩላቸው ኢትዮጵያ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን በመከላከልና የፍልሰት ተጎጂዎችን በመደገፍና መልሶ በማቋቋም እያደረገች ያለችውን ጥረት አድነቀው፣ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት( IOM)ኢትዮጵያ የተመላሽ ዜጎችን ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ጋር በተያያዘ ለምትሠራውን ስራ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
ምንጭ ፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

More Stories
ለህብረተሰቡ የላቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከወረቀት ነፃ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ
በቀጣይ አወንታዊ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ በመከተል ይሰራል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ ገለፁ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2019 የትምህርት ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ነዉ