የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስፖርት ምክር ቤት የ1ኛ ዙር መስራች ጉባኤውን በወላይታ ሶዶ ከተማ ማካሄድ ጀመረ
የስፖርት ምክር ቤትቱ የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀሙንም እየገመገመ ነው ።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስፖርት ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ይገዙን ጨምሮ የፌደሬሽንና የስፖርት ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በአዲሱ ክልል የመጀመሪያ ዙር መስራች ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ምክር ቤቱ አደረጃጀቱን የሀብት አሰባሰብን የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን እንዲሁም ውድድርና የስልጠና ማዕከላት ግንባታ ላይ የታዩ ለውጦች ይገመገማሉ።
በዕለቱ የደቡብ ኢትዮጵያ የስፖርት ምክር ቤት ማቋቋሚያ የመተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ የውሎ አበል የሙያ አበልና የላብ መተኪያ ክፍያዎች መመሪያ ይፀድቃል።
ዘጋቢ ፡ ባዬ በልስቲ
More Stories
አርብቶ አደሩን ከእንስሳት ሀብት ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእንስሳት ኤክስፖርት ማዕከላት እንደሚያስፈልጉ ተጠቆመ
በጌዴኦ ዞን የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ