ምርታማነት በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ቢሮ ገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ቢሮው በክልሉ ለተውጣጡ ባለሙያዎችና ባለ ድርሻ አካላት በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አተገባበር ላይ በአርባ ምንጭ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በICT ዘርፍ አምስቱን የእድገት ተኮር ተግባራትን ለማሳካት በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ ፣ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ አተገባበር፣ በውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ትግበራና በሪፓርት አዘገጃጀትና አስፈላጊነት ላይ ለባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳብ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ ኢትዮጵያን ወደ አደጉት ሀገራት ተርታ ለማድረስ በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እየተሰሩ ካሉ በርካታ ስራዎች መካከል የሳይንስ ሙዝየምና አርተፍሻል ኢንተሌጀንሲ ለአብነት ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉን ሀብት በመለየት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑ ወይዘሮ እመቤት ተናግረዋል።
ጊዜን ገንዘብና ጉልበትን በመቆጠብ በተቋማት በበይነ መረብ ውይይት የተበላሹ የICT መሳሪያዎች ጥገና እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኀላፊ አቶ ዘላለም ጳውሎስ በክልሉ ያለውን ሀብት በሚገባ በመለየት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን በማጠናከር በቴክኖሎጂ ሽግግር የተሻለ ክልል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ያሉ በርካታ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች የባለቤትነት መብት እንድያገኙ የመደገፍና ማበረታታት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሰለሞን ኪዳኔ በበኩላቸው የእዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ ቅጂ በንግድ ምልክት፣ በፓተንት ራይትና ተዛማች መብቶችና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መስራት ይገባል ብለዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አቶ ካምባታ ካቤ በክትትልና ግብረ መልስ አሰጣጥ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር የተሻለ ስራ በዘርፉ መሰራት አለበት ሲሉ ገልጸዋል ።
ስልጠናውን ከተካፈሉት መካከል አቶ ያዕቆብ ማሞ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች ተመዝግበው ጥቅም ላይ እንዲውሉ በሚደረገው ስራ ከስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ችለናል ብለዋል።
ዘጋቢ ፡ ማስረሻ ዘውዴ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ
የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ
እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ