ለህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል – የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

ለህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል – የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

ለህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለፀ።

መምሪያው ከወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016 ዓመት በጀት ዓመት የ1ኛ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን በዚህ ወቅት እንደገለፁት የህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን ለማሳደግና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

ሀላፊው አክለዉም የሚዲያ ዓላማ ወቅታዊ፣ ተዓማኒና ሚዛናዊ የሆነ መረጃን በማሰባሰብ የዞኑ ህዝብ የመረጃ ፍላጎት ለማሟላትና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ተቋማት ጥራት ያለው የሚዲያ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ የሚዲያ ቁሳቁሶች እና ሌሎችም የግብዓት ችግሮች ለመቅረፍም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የወልቂጤ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተወካይ አቶ ተረፈ ሀብቴ መምሪያው በኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ ተመራጭ የመረጃ ምንጭ ለመሆን በየደረጃው እያከናወነ ያለውን ተግባር በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።

ሚዲያ በተለይም የማህበረሱን ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው የጠቆሙት አቶ ተረፈ በመሆኑም መምሪያውና በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮቹ ከጣቢያችን ጋር በዘርፉ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በማሳደግ ለማህበረሰባዊ ለውጥ በጋራ ልንተጋ ይገባል ነው ያሉት።

የወልቂጤ ቅርንጫፍ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የመረጃ አማራጮች እንዳሉት በማንሳት ይህንኑ በመጠቀምም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

በውይይት መድረኩም የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም በተለይም የማህበረሱን እሴትና ባህል በመጠበቅና በመንከባከብ አብሮነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በተለይም ከህዝብ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካል የማሳወቅና የማስረዳት ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የተቋሙ ዋነኛ ችግሮች የሰው ሀይልና የሚዲያ ስራ የሚሰራባቸው ቁሳቁሶች ያለመሟላት መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይ መሠል ችግሮች ለመፍታት ተቀኛጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ምትኬ ገ/ወልድ – ከወልቂጤ ጣቢያችን