የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ወደ ስኮትላንድ ተሸኘ
በ19ኛዉ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን እኩለ ቀን ላይ ውድድሩ ወደሚካሄድበት ግላስኮው ሲያቀና በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አሸኛኘት ተደርጎለታል።
በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የፌደሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ ተገኝተዋል።
የፊታችን አርብ መካሄድ በሚጀምረው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ8 ሴት እና በ6 ወንድ አትሌቶች ትወከላለች።
ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት በሰርቢያ ቤልግሬድ ላይ በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር ላይ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 መዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው