በአፍሪካ አገር አቋራጭ በወጣት ሴት ዘርፍ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ-5ኛ ደረጃ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
ሀዋሳ፡ የካቲት 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአፍሪካ አገር አቋራጭ በወጣት ሴት ዘርፍ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ-5ኛ ደረጃ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል፡፡
በቱኒዚያ ሃማማት በመካሄድ ላይ በሚገኘው 6ኛዉ የአፍሪካ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ-5ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
ውድድሩን ሮቤ ዲዳ በአንደኝነት፣ የኔነሽ ሽመክት 2ኛ፣ ትነበብ አስረስ 3ኛ፣ መቅደስ ዓለምእሸት 4ኛ እና ኮከቤ አበራ 5ኛ በመውጣት ርቀቱን በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።
በሌሎች ርቀቶች በአዋቂ ሴት 10 ኪሎ ሜትር ደጊቱ አዝመራ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ፥ በአዋቂ ወንድ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ገመቹ ዲዳ 3ኛ ወጥቷል።
በወጣት ወንድ 8 ኪሎ ሜትር ሃጎስ እዮብ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው