የጋሞ ዞን መላ ጨዋታ ውድድር በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ

የጋሞ ዞን መላ ጨዋታ ውድድር በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ

የጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ማዜ ሸቀኔ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳሉት ውድድሩ በዞኑ ባሉ 13 ወረዳዎችና 6 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ስፖርተኞች የሚሳተፉ ሲሆኑ እግር ኳስን ጨምሮ የተለያዩ የባህል ስፖርት ውድድር ይካሄዳል ነው ያሉት።

እሰከ መጋቢት 2 የሚቆየው ስፖርታዊ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነትቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ስፖርትን ባህል ያደረገ ማህበረሰብ ጤናማ እንደመሆኑ መጠን ልማትን ከማፋጠን አኳያ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል።

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በበኩላቸው እኛ የምንታወቀው በሰላም ነው ፀብን በእርጥብ ሣር የምናበርድ በመሆናችን ስፖርታዊ ውድድሩን ስናካሂድ በመልካም ጨዋነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ልሣነወርቅ ካሣዬ በበኩላቸው ስፖርት ከወዳጅነት ባለፈ ለኢኮኖሚው ጠቀሜታ እየሰጠ መጥቷል ብለዋል።

የስፖርት አመራሮችና ባለሙያዎች ዞኑን የሚመጥን ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

በመክፈቻ ውድድሩ ላይ የአርባምንጭና የሰላምበር ከተሞች የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ተካሂዷል።

በተመሳሳይም የወንዶችና የሴቶች የ100 ሜትር የሩጫ ውድድርም ተደርጓል ።

ዘጋቢ ፡ ታምሩ በልሁ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን