የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ የካቲት 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ ጉባኤውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት፥ ምክር ቤቱ በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ በ5 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ብለዋል።
በጉባኤው የ2018 በጀት አመት የአስፈጻሚ አካላት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ዝርዝር ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ አስቀድሞ የ6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ የጀመረ ሲሆን፥ በግብርና፣ በመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ እድል ፈጠራና በገቢ አሠባሰብ እንዲሁም በሌሎች ሴክተሮች አፈጻጸም ዙሪያ በተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ይመክራል።
6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ከወጣው መርሐ ግብር መረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው