የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ በማከናወን የዞኑን ሁለንተናዊና ዘለቄታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተገለጸ

የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ በማከናወን የዞኑን ሁለንተናዊና ዘለቄታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ የካቲት 19/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ በማከናወን የዞኑን ሁለንተናዊና ዘለቄታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኮንታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የ2016 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ግማሽ ዓመት የሥራ ሪፖርት ያቀረቡት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ በማከናወን የዞኑን ሁለንተናዊና ዘለቄታዊ ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል።

በኢኮኖሚ መስክ የግብርና ልማትን ለማሳደግ በሚያስችሉ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ለውጥ ማሳየት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ከፍተኛ ዝናብ ሰብል ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረስ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ መሠረተ ልማት የዘጎችን ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች የሚገነቡበት ዞን በመሆኑ ሠላማዊ የሥራ አከባቢን መፍጠር፣ በአስፈፃሚ መ/ቤቶች የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን ለዞኑ ምክር ቤት አቅርበዋል።

ከእቅድ በላይ የተከናወኑ እንዲሁም የአፈፃፀም ውስንነት ያለባቸው ተቋማት እንዳሉ በሪፖርቱ ቀርቧል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማረ ትውልድ ለማፍራት አዳሪ ትምህርት ቤት በመገንባት የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት በተሠሩ ስራዎች የላቀ ውጤት እንደነበር በሪፖርቱ ተጠቁሟል።

የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማርካት ከዘጎች የሚሰበሰበው መደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከዕቅድ በላይ መሆኑ ለሁለንተናዊና ዘለቄታዊ ዕድገት አይነተኛ አስተዋጽኦ መኖሩ በሪፖርቱ ተገልጿል።

በተለያዩ ዘርፎች ያሉ አፈጻጸሞች በትምህርት፤ በጤና፤ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በቱሪዝም፤ እንዲሁም ሙስናን በመዋጋት የነበሩ ክንውኖችና ሌሎችም ቀርበዋል።

ዘጋቢ፡ አብዮት እሸቱ – ከዋካ ጣቢያችን