የተማሪዎች ምገባ መጀመር ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርት አንዲከታተሉ አስችሏል- የሣላማጐ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
የሳላማጐ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባንታየሁ መለሰ እንደገለጹት በአለም ምግብ ኘሮግራም በወረዳዉ 24 ትምህርት ቤቶች መደበኛ እና ፍሬሽ ምግቦችን የሚጠቀሙ ሲሆን በአጠቃላይ ወንድ 5ሺ 394 ሴት 4 ሺህ 8 62 በድምሩ 10 ሺህ 256 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሃና መጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ሣይክል ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ተሻገር ወርቁ የዚህ ኘሮግራም መጀመር በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራን ውጤታማ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ የሒሳብ አስተማሪ የሆኑት መምህር ማሙሽ ጥጋቡም የዚህ ምገባ ኘሮግራም መጀመር በትምህርት ቤቱ የተማሪ ዉጤት ላይ መሻሻል መታየቱን ተናግረዋል፡፡
ተማሪ ልዩ ሳካና ተማሪ ብዙአየሁ አልማየሁ በጋራ በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሳይመገቡ መተው እንደሚጨነቁና ለትምህርታቸው ትኩረት እንደማይሰጡ ገልፀው አሁን ግን በአግባቡ እየተከታተሉ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ዘጋቢ፡ደፋሩ ስፍታዬ- ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
አርብቶ አደሩን ከእንስሳት ሀብት ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእንስሳት ኤክስፖርት ማዕከላት እንደሚያስፈልጉ ተጠቆመ
በጌዴኦ ዞን የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ