በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ማቴዎስ አኒዮ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አድርገው ሾመ
ሀዋሳ፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ማቴዎስ አኒዮ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አድርገው ሾሟል::
አቶ ማቴዎስ አኒዮ ከወረዳ እስከ ክልል ባሉ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ባገለገሉበት ወቅት በብቃትና በታማኝነት ማገልገላቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፖርቲ አቶ ይግለጡ አብዛ ገልፀዋል፡፡
በዚሁ መሰረት ጉባኤውም አቶ ማቴዎስ አኒዮን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
ዘጋቢ፡ በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/