የከምባታ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዶ/ር ዳዊት ለገሰን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ

የከምባታ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዶ/ር ዳዊት ለገሰን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ

ሀዋሳ፡ የካቲት 18/2016 ዓ፣ም (ደሬቴድ) የከምባታ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ዶ/ር ዳዊት ለገሰን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የዞኑ ምክር ቤት ባካሄደው በአስቸኳይ ስብሰባው ዶ/ር ዳዊት  ለገሰን የዞኑ አስተዳዳሪ እንዲሆኑ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው ዶ/ር ዳዊት ለገሰ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ኤክስኪዩቲቭ ቺፍ ዳይሬክተር፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ ተባባሪ ዲን፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች አስተባባሪ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ክፍል አስተባባሪ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ሬጅስትራር  እንዲሁም በዋቸሞ እና በሀዋሳ ዩኒቨርስቲዎች የ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በማስተማር መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ የፈፀሙት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዳዊት ለገሰ ባደረጉት ንግግር  ዞኑ ያለውን ፀጋ በመጠቀም ለነዋሪው የተሻለ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፃ በገቢ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እንዲሁም በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ አቶ ተክሌ ስዩም የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ እና አቶ ተሻለ ዩሐንስን ምክትል አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ዘጋቢ፡ ቃልአብ ፀጋዬ