በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪል ማህበራት በመንግስት ያልተሻፈኑ በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰሩ ነው – የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪል ማህበራት በመንግስት ያልተሻፈኑ በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰሩ ነው – የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ

ሀዋሳ፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪል ማህበራት በመንግስት ያልተሻፈኑ በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ::

BBBC (ቦሌ መጽሐፍቅዱስ መጥመቃዊያን ቤተክርስቲያን) የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ እና ጉራጌ ዞኖች ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመስራት የትውውቅ መድረክ ከባለድርሻ አካላት  ጋር በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል::

BBBC (ቦሌ መጽሐፍቅዱስ መጥመቃዊያን ቤተክርስቲያን) የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ከድርጅቱ ባለድርሻ አካላት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ ከበደ ወልደጊዮርጊስ የቦሌ መጽሀፍ ቅዱስ መጥመቃዊያን የህጻናት እንክብካቤና የህብረተሰብ ልማት ዳይሬክተር ሲሆኑ በሀገር በአገር አቀፍ ደረጃ በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና በንጹህ ውሃ ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል::

ከተመሠረተ ሃምሳ ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ድርጅቱ በመንግስት ያልተሸፈኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየሰራ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉንም አቶ ከበደ ጠቁመዋል::

አቶ አብዲታ ታደሰ የBBBC ቦሌ መጽሀፍ ቅዱስ መጥመቃዊያን ቤተክርስቲያን የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት የሹርሞ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ድርጅቱ መቀመጫውን አውስትራሊያ ካደረገው ድርጅት ጋር በመተባበር በትምህርት በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ያለው ድርጅት ነው ብለዋል::

ድርጅቱ በሃዲያና ጉራጌ ዞኖች በሁለት ወረዳዎች እንደሚሰራ የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወን መሆኑንና ከአንድ መቶ ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነም አቶ አብዲታ ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቶቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ስራ አስኪያጁ ጥሪ አቅረበዋል::

በትውውቅ ፕሮግራም ላይ የተገኙት አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው በመንግስት ያልተሸፈኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመሸፈን ረገድ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና የጎላ እንደሆነ አንስተዋል::

በወቅቱ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፊሲካል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አክሊሉ መኔዶ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን በርካታ ስራዎችን ክልሉ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በመንግስት ያልተሸፈኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በሲቪል ማህበረሰብ ልማት ድርጅቶች እየተሸፈኑ መሆናቸውን ገልጸዋል::

ክልሉ በአዲስ ከተመሠረተ ወዲህ 22 የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ስራ መጀመራቸውን የተናገሩት አቶ አክሊሉ ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር (8 መቶ ሚሊየን) ብር በላይ ካፒታል ይዞ የተለያዩ የልማት ራዎችን እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል::

ትውውቅ የተደረገው BBBC ፕሮጀክት የተለያዩ የብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ይዞ ስራ መጀመሩንም አቶ አክሊሉ አንስተዋል::

ዘጋቢ፡ በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን