በኢፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተመራጮች አርባምንጭ ከተማ ገቡ
ሀዋሳ፡ የካቲት 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተመራጮች አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 49 አባላት አርባምንጭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወሮ ፀሐይ ወራሳ እና በጋሞ አባቶች የተመራ ልዑክ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ተወካዮቹ በቀጣይ ወደ ምርጫ ክልላቸው በመሄድ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የህዝብ ተወካዮች ከመረጧቸው ህዝብ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በዓመት 2 ጊዜ ውይይት እንዲያደርጉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ ይደነግጋል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ