ሀዋሳ፡ የካቲት 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሰላምና ልማትን በማስተሳሰር የብልጽግና ጉዞ እዉን ማድረግ እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ ተናገሩ፡
“ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በየም ዞን ሣጃ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ በሕዝብ መድረኮች የህዝብ ጥያቄዎችና የተወሰዱ መፍትሄዎች የሚል ሰነድ ቀርቧል፡፡
ሰነዱን ያቀረቡት የሣጃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጌታሁን ካሳሁን በተለያዩ መድረኮች ላይ በሕዝብ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አብዛኛዉ ምላሽ ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
በከተማው 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የመንገድ ዳር መብራት ችግርን መቅረፍ መቻሉንና በ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለፈርጀ ሦስት ከተማ የሚመጥን የቄራ አገልግሎት የሚሰጥ ግንባታ ተገንብቷል ብለዋል።
የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል የሰንበት ገበያ መቋቋሙንና ወጣቶችን በማደራጀትም የከተማ ፅዳትና ዉበት የማስጠበቅ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በመብራት፣ ውሃና መንገድ እንዲሁም የሰላም ጉዳዮች ላይ መስተካከል ይገባቸዋል ያሏቸዉን ሃሳቦች አንስተዋል፡፡
ከተሳታፈዎች የቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡት የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ገ/ሚካኤል የዉሃ፣ የመብራትና የመንገድ ጉዳዮች ለማስተካከል ከክልሉ ጋር በጋራ እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡
የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥም የሁሉም አካላት ሚና የጎላ ነዉ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡
ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ልማት እንዳይሰራ የሚያደናቅፉ አካላት ካሉ ተከታትሎ ሕጋዊ እርምጃ ለመዉሰድ ዝግጁ መሆናቸዉን አስረድተዋል፡፡
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው ሰላም እና ልማትን በማስተሳሰር የብልፅግና ጉዞ እዉን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የወጣቱን ስራ አጥነት ችግር ለመፍታትም ህበረተሰቡ ከመንግሰት ጎን መሆን እንዳለበትም አመላክተዋል ፡፡
በውይይት መድረኩ የተነሱ ሀሳቦችን ወደ ለክልሉ መንግስት በማድረስ በቅደም ተከተል ከሌሎች አካባቢዎች ጋር እኩል እንዲለማ እናደርጋለን ብለዋል ፡፡
ዘጋቢ ፣ ማሙዬ ፊጣ- ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የማህበረሰቡን አንድነት፣ ሠላምና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ባህላዊ እሴቶችን ጠብቆ በማቆየት ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
በክህሎት ፣ በቴክኖሎጂና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ