“እኔ ለሃገሬ የሠላም ዘብ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በዲላ ከተማ የወጣቶች ውይይት መደረክ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ የካቲት 09/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “እኔ ለሃገሬ የሠላም ዘብ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በዲላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አባላት ለተጽዕኖ ፈጣሪ እና ለምሁራን ወጣቶች የተዘጋጀ የውይይት መደረክ አካሂዷል።
የውይይት መደረኩን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ፥ እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ዞን በነበሩት እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎች ወጣቶች ሲያበረክቱ የቆዩት አበርክቶ ከፍተኛ እንደነበረ ገልጸው፥ በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ተሳትፎአቸውን ያላማከለ እንቅስቃሴ ውጤታማ ስለማይሆን ከወጣቶች ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዩኤል ተሾመ ወጣቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ወንድማማችነትንና እህታማማችነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለሠላም ዘብ እንዲቆሙ አሳስበዋል።
በመድረኩም የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አባላት ለተጽዕኖ ፈጣሪ አና ለምሁራን ወጣቶች የዞን፣ የክልልና የፓርቲው የወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ በኣሪ ዞን ጋዘር ከተማ አካሄዱ
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ እና በላሃ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ ሕዝባዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ተካሄደ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል