ከ64 ዓመታት በኋላ ፈረንሳይን በሜዳዋ ማሸነፍ የቻለችው ጣሊያን
በአውሮፓ ሀገራት እግር ኳስ ታላላቅ ተቀናቃኞች በተገናኙበት የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ፣ ጣሊያን በሜዳዋ ፈረንሳይን 3ለ1 በማሸነፍ የ64 ዓመታት የረጅም ጊዜ የሜዳ ላይ የድል ድርቋን ሰብራለች።
ትናንት ምሽት በታሪካዊው የጁሴፔ ሜአዛ (ሳንሲሮ) ስታዲየም በተካሄደው እና ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ጨዋታ፣ እንግዳዋ ፈረንሳይ ጨዋታውን በጠንካራ ሁኔታ በመጀመር ገና በ10ኛው ደቂቃ በሚሼል ኦሊሴ ጎል መሪ መሆን ችላ ነበር።
ይሁን እንጂ በሜዳዋና ደጋፊዎቿ ፊት የተጫወተችው ጣሊያን ቀድሞ በተቆጠረባት ግብ ሳትደናገጥ ወደ ጨዋታው በፍጥነት ተመልሳለች።
ለ”አዙሪዎቹ” ወጣቱ አጥቂ ፒዬ እስፖሲቶ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ አማካዩ ዳቪዴ ፍራቴሲ ተጨማሪ ጎል አክሎ ጣሊያን ከመመራት ተነስታ አስደናቂ ድል እንድትቀዳጅ አስችለዋል።
ይህ ውጤት ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ በገዛ ሜዳው ፈረንሳይን ማሸነፍ ያልቻለበትን ታሪክ የቀየረ ትልቅ ድል ሆኖ ተመዝግቧል።
በአንጻሩ፣ በአዲሱ አሰልጣኟ ዚኔዲን ዚዳን እየተመራች ወደ ሜዳ የገባችው ፈረንሳይ፣ በአሰልጣኙ የስልጣን ዘመን የመጀመሪያ ሽንፈቷን ለመቅመስ ተገዳለች።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ከ64 ዓመታት በኋላ ፈረንሳይን በሜዳዋ ማሸነፍ የቻለችው ጣሊያን

More Stories
ኢትዮጵያ ሞዛምቢክን አሸነፈች
ማንቸስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ
20 የሊግ ዋንጫዎችን በሦስት አሰልጣኞች ብቻ