ኢትዮጵያ ሞዛምቢክን አሸነፈች

ኢትዮጵያ ሞዛምቢክን አሸነፈች

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 3ኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ ሞዛምቢክን 1 ለ 0 በማሸነፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ድሏን አሳክታለች።

ማፑቶ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለዋሊያዎቹ ወሳኟን የማሸነፊያ ጎል ከነዓን ማርክነህ በሁለተኛው አጋማሽ አስገኝቷል።

ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተከትሎ 3 ነጥብ በመያዝ በምድቧ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ማክሰኞ ባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ላይ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ