ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ፊርማቸውን አኖሩ!

ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ፊርማቸውን አኖሩ!

አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የእንግሊዙን ታላቅ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት የሚያስችላቸውን ውል ተፈራርመዋል።

ፋብሪዚዮ ሮማኖ ይዞት በወጣው መረጃ መሠረት፣ የውል ስምምነት ሰነዶቹ ተልከው በሁለቱም ወገኖች ፊርማ ጸድቀዋል።

የ54 ዓመቱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ከዩናይትድ ጋር የሁለት ዓመት ተኩል ኮንትራት መፈራረማቸው ተገልጿል።

ማንቸስተር ዩናይትድም ፖቼቲኖን የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን በዚህ ሳምንት መጨረሻ (ቅዳሜ ወይም እሁድ) በይፋ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።

በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ፖቼቲኖ፣ ወደ እንግሊዝ ከማቅናታቸው በፊት ብሔራዊ ቡድናቸውን በሚቀጥሉት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ይመራሉ።

እነዚህን ሁለት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እንዳጠናቀቁም፣ በመጪው ሳምንት ወደ ማንቸስተር በመብረር በኦልድ ትራፎርድ አዲሱን የአሰልጣኝነት ምዕራፋቸውን በይፋ ይጀምራሉ።

ይህ ሹመት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም ሆትስፐርን እና ቼልሲን በማሰልጠን ሰፊ ልምድ ያካበቱት ፖቼቲኖ፣ ማንቸስተር ዩናይትድን ወደ ቀድሞ ገናናነቱ ይመልሱታል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ