ማንቸስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ
ማንቸስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን በይፋ አስታውቋል።
አሰልጣኙ ከመጪው ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በኦልድ ትራፎርድ ስራቸውን በይፋ ይጀምራሉ።
ማንቸስተር ዩናይትድ ፖቼቲኖን እና የአሰልጣኝ ቡድናቸውን ለማስፈረም ከአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጿል።
በዚህም መሰረት ፖቼቲኖ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያላቸውን ኃላፊነት እንዳጠናቀቁ ወደ ማንቸስተር የሚያቀኑ ይሆናል።
በከፍተኛ ፍጥነት እና በማጥቃት ላይ በተመሰረተው የአጨዋወት ዘይቤያቸው የሚታወቁት ፖቼቲኖ፤ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ቡድን በመገንባት እንዲሁም ወጣት ተጫዋቾችን በማብቃት ረገድ ትልቅ ስም ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው።
ፖቼቲኖ የአሰልጣኝነት ህይወታቸውን እ.ኤ.አ በ2009 በስፔኑ ኢስፓኞል የጀመሩ ሲሆን፤ በመቀጠልም ወደ እንግሊዝ በማምራት በ2014 ሳውዝሃምፕተን በፕሪሚየር ሊጉ ታሪኩ ከፍተኛውን ነጥብ እንዲያስመዘግብ አስችለዋል።
በመቀጠል በቶተንሃም ባሳለፏቸው አምስት ሙሉ የውድድር ዘመናት ክለቡን በተከታታይ ለአራት ጊዜያት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ከማድረጋቸውም በላይ፣ በ2019 ክለቡን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አብቅተዋል።
በ2021 የፈረንሳዩን ፒኤስጂ በመቀላቀል የሊግ 1 ዋንጫን፣ የፈረንሳይ ዋንጫ እና የትሮፌ ዴ ሻምፒዮንስን አሸንፈዋል።
በ2023 ደግሞ ወደ እንግሊዝ ተመልሰው ቼልሲን አሰልጥነዋል።
በቅርቡም የአሜሪካ ወንዶች ብሔራዊ ቡድንን በመምራት በፊፋ የዓለም ዋንጫ እስከ ጥሎ ማለፍ (16 ውስጥ) ድረስ ማድረስ ችለዋል።
የፖቼቲኖ ወደ ኦልድ ትራፎርድ መምጣት በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት አዲስ የስኬት ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ማንቸስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ

More Stories
ኢትዮጵያ ሞዛምቢክን አሸነፈች
20 የሊግ ዋንጫዎችን በሦስት አሰልጣኞች ብቻ
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ፊርማቸውን አኖሩ!