“የዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አሰተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ቀን በጎፋ እና በወላይታ ዞኖች በድምቀት ተከብሯል
የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማልማትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንቱ መልኩ እንዳሉት፤ የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ ሲከበር በክልላችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተከብሯል።
በቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት አድርጎ በመስራት የተፈጥሮ ሀብት፣ የታሪክ እና የባህል ትውፊቶችን በማስተዋወቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎቻችንን ማሳደግ እንደሚቻል ተገለጿል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት መና ከዞኑ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ የዳሞት ፀዳል ተራራ በማልማት ለጎብኝዎች ምቹ በማድረግ ባህላዊ እሴቶች ለመላው የአለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጎፋ ዞን የቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ያዕቆብ፤ በጎፋ ዞን በርካታ ለቱሪዝም ምቹ የተፈጥሮ ፀጋዎች መኖራቸውን ገልፀው የሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በመምጣት መጎበኘት የሚችሉ ቱሪስቶችን በመሳብ ዘርፉን በማስፋፋት በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የየም ብሔረሰብ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ የ”ሄቦ” በዓል የተራራቀ የሚገናኝበት የአዲስ ዓመት መጀመሪያ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ አስታወቁ
ሠላምን በማጽናት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ
የደም ልገሳ ፕሮግራም ህይወትን የማዳን ትልቅ ዘመቻ መሆኑ ተገለፀ