የየም ብሔረሰብ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ የ”ሄቦ” በዓል የተራራቀ የሚገናኝበት የአዲስ ዓመት መጀመሪያ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ አስታወቁ
የየም ብሔረሰብ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ የ”ሄቦ” በዓል ሲምፖዚየም በዞኑ ሳጃ ከተማ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የሄቦ በዓል የረጅም ዘመን የብሔረሰቡ የታሪክ አካል መሆኑን የጠቀሱት የየም ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ፤ የሄቦ በዓል ከጭጋግና ጨለማ ወደ ብርሃንና ዓዲስ ዓመት መሸጋገሪያ፤ የእርቅ የሰላምና የአዲስ ተስፋ ማብሰሪያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሄቦ በዓል ከመስከረም 14 ጀምሮ እንደሚከበር የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪዉ፤ በየዓመቱ የሚደረገዉ ሲምፖዚየም በዓሉንና ታሪክ ለቀጣይ ትዉልድ ለማሰተላለፍ ትልቅ መሰረት ነዉ ብለዋል፡፡
ትስስርን በመፍጠርና በአንድነት በመቆም ለቀጣዩ ልማት የሚታሰብበት በዓል እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪዉ ገልፀዋል፡፡
በሲምፖዚየሙ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢዉ ህብረተሰብ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
በነገዉ ዕለት የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በዞኑ ሳጃ ከተማ በአደባባይ የሚከበር ይሆናል፡፡
የበዓሉ ዝግጅት በነገዉ ዕለት በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ይተላለፋል፡፡
ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ

More Stories
“የዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አሰተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ቀን በጎፋ እና በወላይታ ዞኖች በድምቀት ተከብሯል
ሠላምን በማጽናት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ
የደም ልገሳ ፕሮግራም ህይወትን የማዳን ትልቅ ዘመቻ መሆኑ ተገለፀ