ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታን ባለማሸነፍ ጉዞው ቀጥሏል

ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታን ባለማሸነፍ ጉዞው ቀጥሏል

የእንግሊዙ ሀያል ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታን ባለማሸነፍ ጉዞው ቀጥሏል።

ክለቡ በ12ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር በሜዳው ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 4ለ0 በሆነ ውጤት ተረቷል።

ለእንግዳው ቡድን ብሬንትፎርድ የማሸነፊያ ግቦችን ካሉም ዊልሰን ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ክርስቶፈር አዬር እና ኬቨን ሻደ ቀሪ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።

በዚህም በአሰልጣኝ ኬዝ አንድሪው የሚመራው ብሬንትፎርድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦልድትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን ማሸነፍ ችሏል።

በተጨማሪም የለንደኑ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉ ከሜዳው ውጪ ከ10 ጨዋታዎች በኋላ ጨዋታን ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋው ዳንጎ ኦታራ ሦስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ዳንጎ ኡታራ ለካለም ዊልሰን ሁለት ግቦችን አመቻችቶ ማቀበሉ፣ በኦልድትራፎርድ በተደረገ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አንድ የእንግዳ ቡድን ተጫዋች ለአንድ የቡድን አጋሩ ሁለት የግብ ኳሶችን (አሲስት) አመቻችቶ ሲያቀብል በታሪክ ለሦስተኛ ጊዜ ብቻ ነው።

ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ 2011 ጄምስ ሚልነር ለማሪዮ ባሎቴሊ እንዲሁም በመስከረም 2024 መሐመድ ሳላህ ለሉዊስ ዲያዝ ይህንን አድርገው ነበር።

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ 12 ጨዋታዎች ግብ ሳያስተናግድ ከሜዳ መውጣት አልቻለም።

ከዚህ በፊት ይህን ያደረጉት በ1930-31 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ዘመን ነበር።

ዩናይትድ በዚህ ዓመት በሁሉም ውድድር 40 ግቦችን አስተናግዷል።

ብሬንትፎርድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 20 በማድረስ 5ኛ ደረጃን ይዟል።

በፕሪሚየር ሊጉ 10 ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያልቻለው እና 6ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ በ8 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ