ከወራጅ ቀጣና ለመውጣት የሚደረግ ትንቅንቅ
በ12ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ውጤት የራቀው እና በከባድ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል።
ጨዋታው ለሁለቱም ቡድኖች ተቃራኒ ግቦችን የያዘ ከባድ ፍልሚያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ እየተመራ የሚገኘው ዩናይትድ፣ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር ባደረገው የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታ በሊቨርፑል 4 ለ 0 ሲሸነፍ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ ከስፖርቲንግ ጋር 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።
ቡድኑ እስካሁን ካደረጋቸው 11 የሊግ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ በማሸነፍ በ19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፤ የዛሬው ድል ከወራጅ ቀጣና ለመውጣት ወሳኝ ነው።
ተጋጣሚው ብሬንትፎርድ በ11 ጨዋታዎች አራት ድል፣ አምስት አቻ እና ሁለት ሽንፈት በማስመዝገብ በ17 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ወጥ ብቃቱን ለማስቀጠል ይፋለማል።
በዕለቱ ከማንቼስተር ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ ጨዋታ በተጨማሪ ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
በዚህም መሰረት በተመሳሳይ ሰዓት መሽት 12 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከ ኮቬንተሪ ሲቲ እንዲሁም ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ኤፕስዊች ታውን ከ አስቶን ቪላ ጋር ይጫወታሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ የአምበሉን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ውል በአንድ ዓመት አራዘመ
የዴክላን ራይስ ትልቁ ውርርድ
ቼልሲ አሌክስ ስኮትን ለማስፈረም ያለው ፍላጎት አሁንም ቀጥሏል