“የፅናት ቀን” በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተከበረ ነው
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጳጉሜ 3 ቀን ”ፅኑ ሀገር ብርቱ መሰረት” በሚል መሪ ቃል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
“የፅናት ቀን” ለሀገረ መንግስት ግንባታ ዋጋ የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ ችግኖች የሚታወሱበት ዕለት ነው።
ኢትዮጵያ በታሪክ ምዕራፎቿ ዳር ድንበር ሳታስደፍር ፀንታ የኖረች ሀገርና የጀግኖች መፍለቂያ ሀገር ናት ሲሉ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ በዚሁ ቀን አከባበር ላይ በመልዕክታቸው አንስተዋል።
ሀገራችን ታሪኳን የሚመጥን ወደፊትም ፈተናዎችን መቋቋም የሚያስችል አቅም እየገነባች ነውም ብለዋል።
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁሉ አቀፍ ለውጦች መመዝገባቸውን የጠቀሱት አፈ ጉባኤዋ በ2019 ዓ.ም ይህን አጠናክሮ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ “ፅናት ሀገርን ያሻግራል”፣ “ፅናት ራዕያችንን ያሳካል”፣ “ፅናት መተማመንን ያጎለብታል” እና መሰል መልዕክቶች ተስተጋብተዋል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንፃ እየተመረቀ ነው
በማህበራት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ
በኮሬ ዞን የጽናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው