በኮሬ ዞን የጽናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

በኮሬ ዞን የጽናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

‎ዘመናዊ ቁመና፣ በሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ ያደገበትን አቅም ማሳየትና ለሀገረ-መንግሥቱ ዘላቂነትና ለሕዝብ ሰላም የተከፈለውን የጀግኖች መስዋዕትነትን በመዘከር ነው የጽናት ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው።

‎በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አገኘሁ በቀለ ለሀገረ-መንግሥቱ ዘላቂነትና ለሕዝብ ሰላም የተከፈለውን የጀግኖች መስዋዕትነትን በመዘከር የጽናት ቀኑ የሚታሰብበት ነው ብለዋል።

አክለውም በጀግና አባቶች ሉአላዊነቷ ተጠብቆ ዛሬ የምንኖርባትን ኢትዮጵያ ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር በጽናት መጋደል እንደሚጠበቅም አቶ አገኘሁ ተናግረዋል።

‎የጽናት ቀኑ የዞኑ አመራሮችና የፀጥታ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን