አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን ለማስፈረም ከጫፍ ደረሰ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል የአስቶንቪላውን የመሐል ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳን በክለቡ ረጅም የዝውውር እቅድ ውስጥ አካቶ ሲከታተለው ከቆየ በኋላ፣ አሁን ላይ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርቧል።
መድፈኞቹ የመስመርና የመሐል ተከላካዮቻቸው ዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪየን ቲምበር በጉዳት ከሜዳ መራቃቸውን ተከትሎ የኋላ ክፍላቸውን ለማጠናከር በዝውውር እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።
ኮንሳ በመሐል ተከላካይነትም ሆነ በቀኝ መስመር ተከላካይነት የመጫወት ከፍተኛ ብቃት ያለው በመሆኑ የክለቡ ዋና ኢላማ ሆኗል።
በሁለቱ ክለቦች ባለቤቶች መካከል የተደረገውን ቀጥተኛ ውይይት ተከትሎ በዋጋ ረገድ የነበረው ልዩነት በመጥበቡ ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
ኮንሳ እ.ኤ.አ በ2019 ከብሬንትፎርድ ከተቀላቀለ ወዲህ 286 ጨዋታዎችን አድርጓል።
ባለፈው የውድድር ዘመን ቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ሲያነሳና በሊጉ 4ኛ ደረጃን ሲይዝ 48 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፏል።
አርሰናል የባየር ሊቨርኩሰኑን ተከላካይ ጃሬል ኳንሳንም በአማራጭነት ሲከታተል የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ የኤዝሪ ኮንሳ ዝውውር ሊጠናቀቅ ይበልጥ ተቃርቧል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ዘ ስፔሻል ዋን” አስቀድመው ያዩት እውነት
ፒኤስጂ ፌራን ቶሬስን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ!
ማርከስ ራሽፎርድ እና እሱን ያገለለው አሰልጣኝ ዳግም ግጥምጥሞሽ