ሌላኛው አፍሪካዊ ተስፋ

ሌላኛው አፍሪካዊ ተስፋ

በፈረኦን ደበበ

በድህነትና ጉስቁልና ትታወቅ የነበረችው አህጉር በልማት ዕድሎች ታጅባ ግስጋሴዋን ቀጥላለች።

አሁን እየመጡ ያሉ ለውጦች የደረሰባትን ጠባሳ እንድትለውጥ ያስችላታል። የህዝቦቿን ኑሮ ያሻሽላሉ፡፡ ብልጽግናን ለማረጋግጥም አቅም ይሆናሉ፡፡ በኃይል ልማት ችግር ምክንያት አንዳንድ ትላልቅ በሚባሉ ሀገራት ሳይቀር የታዩ ቀውሶች ሥጋት ፈጥረው ነበር፡፡

ይህንን ለመከላከል ከአብራኳ ተገኝተው በልጆቿና በአጋር አካላት ጥረት እውን ይሆናሉ የተባሉ ፕሮጀክቶች ተስፋ አንጥቀዋል፡፡ ከዓመታት በፊት ተጠንስሶ አሁን ወደ መተግበሪያ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለው የኃይል ማመንጫ ግድብ “ታላቁ የኢንጋ የውኃ ኃይል ማመንጫ” ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን የሚገነባውም በታላቁ የኮንጎ ወንዝ ላይ ነው፡፡

በርካታ የአካባቢው ሀገራት ድርሻ እንዳላቸው የተነገረለትን ፕሮጀክት ለመደገፍ የውጭ ኩባኒያዎችም ተነሳስተዋል፡፡ጅምር ጥረታቸው በሚያደርጉት ተጨባጭ ተሳትፎ የሚወሰን ቢሆንም፡፡ የስም አወጣጡና ጠቀሜታው ከሀገራችን ታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር የሚመሳሰለው ፕሮጀክቱ 42 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሌላኛው አፍሪካዊ ተስፋ ኃይል ማመንጨት አቅም ሲኖረው የግንባታ ወጪው 80 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅም ተገልጿል በዓለም ላይ በግዙፍነቱ ታዋቂ የሆነውንና በቻይና የሚገኘውን “ስሪ ጎርጅስ” ግድብን ሁለት እጥፍ በመብለጥ፡፡

ይህን ያህል ሀብት በአፍሪካ እምብርት መገኘቱ ዜጎችን ሲያኮራ በማዕድን ሀብት በበለጸገችው በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሆኑ ደግሞ እጥፍ ድርብ ያደርገዋል። በኃይል እጥረት ምክንያት ወደ ውጥረት እየገቡ ላሉ ደቡብ አፍሪካ ለመሳሰሉ ሀገራትም ተስፋ ሰጥቷል፡፡

ከዓመታት ቀደም ብሎ ሲደረግ የነበረውን የፕሮጀክት ጥናት ተከትሎ ሰሞኑን የተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ የቆዩ ሲሆን ጊዜው እንደ ኬኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ባሉ ሀገራት ላለው ህዝባዊ ተቃውሞም መልስ የሚሰጥ ነው፡፡ ልማትን ፈልጋችሁ የተነሳችሁ ሁሉ “አይዟችሁ፤ እኔ አለሁላችሁ” እንደማለት፡፡ በስድስት ደረጃዎች ግንባታው ይካሄዳል የተባለለት የኢንጋ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ቀደም ብሎ በእ.ኤ.አ. 1972 እና በ1982 በወንዙ ላይ በተሠሩ ኢንጋ 1 እና ኢንጋ 2 የተባሉ ግድቦች አካል ሲሆን እነዚያ ያመነጩት የነበረው የኃይል መጠንም በቅደም ተከተል 351 እና 1424 ሜጋ ዋት ነበር፡፡

ያለውን የገበያ ዋጋ እና የገንዘብ ምንጮችን ታሳቢ በማድረግ ቅርጹም ተሻሽሎ ሊሠራ ይችላል የተባለለት የኢንጋ 3 ግዙፍ ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ በንድፍ ደረጃ ሲሆን መገኛውም በምዕራባዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሆኑን “ባንክትር 20k” የተባለ ድረ-ገጽ ጠቅሷል፡፡ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለአፍሪካና ለአውሮፓ ማድረስ የሚችል መሆኑንም በመጠቆም፡፡ የቻይና፣ ስፔንና ሌሎች ሀገራት ኩባኒያዎች ከዴሞክራቲክ ኮንጎ መንግሥት ጋር ውል በመግባት የጥናት ሥራዎችን አካሂደዋል የተባለለት ፕሮጀክት የአካባቢው ሀገራት ድርሻንም የያዘ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ከ11 ሺህ ሜጋ ዋት ላይ ደቡብ አፍሪካ 5000፣ ናይጄሪያ 3000፣ በኮንጎ ማዕድን የሚያወጡ ኩባኒያዎች 1 ሺህ 300፣ ጊኒ 7ሺህ 500 እንዲሁም ቀሪው ለዴሞክራቲክ ኮንጎ ሀገራዊ አገልግሎት እንደሚውል የአፍሪካ ህብረት ገልጿል፡፡ ዊክፔዲያ የተባለው የመረጃ ምንጭም በበኩሉ ግድቡ በኮንጎ ወንዝ ላይ ባለው ኢንጋ ፏፏቴ ላይ እንደሚገነባ ጠቁሞ በዓለም ላይ ወደር ያልተገኘለት የኃይል ማመንጫ መሆኑንም አስታውቋል ከዋና ከተማዋ ክንሻሳ በ225 ኪ.ሜትር ወይም በ142 ማይሎች ላይ መገኘቱን በማስታወቅ፡፡

ቡንዲ ከተባለው ወንዝ በስተደቡብ ግድቡ ከኮንጎ ጋር እንደሚገናኝና ኋላም ኮንጎ ወንዝን በመቀልበስ ከሰሜን በኩል ትልቅ የሰው ሠራሽ ሀይቅ ለመፍጠር እንደሚረዳ ጠቁሞ እያንዳንዱ ሰባቱ ግድቦች በተለያዩ ባለሀብቶች መያዛቸውንም ገልጿል፡፡

የዓለም ባንክ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና ዋና የገንዘብ ምንጮች መሆናቸውን በመጠቆም፡፡ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ” የተባለው ድረ ገጽ በበኩሉ ዓላማውን በዝርዝር ሲያብራራ አህጉር አቀፍ የሆነ የኃይል ልማት ለማምጣት እንደሚረዳ ጠቁሞ ለዚህ ቅድሚያ የሚወስዱት ደግሞ አፍሪካዊ የልማት ድርጅቶች ናቸው ብሏል፡፡

ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል የአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት ወይም ኔፓድ፣ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ፣ የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል እና ”እስኮስ“ የተባሉ የአፍሪካ ትላልቅ የኃይል ተጠቃሚዎች ናቸው ብሏል። የኮንጎ ወንዝ ወደ አትላንቲክ ውቂያኖስ በሚገባበት ዱካ ላይ እንደሚገነባ ጠቁሞ በ6 ደረጃዎች የሚሠራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል ወንዙ ወደ ውቂያኖስ ከሚገባበት ቦታ 50 ኪ.ሜትር ከፍ ብሎ እንደሚገነባ ጠቁሞ ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ክንሻሳም 225 ኪ.ሜትር ወይም 140 ማይልስ ደቡብ ምዕራብ መሆኑን ገልጿል፡፡ ግዙፍነቱ በሰኮንድ 42 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሰት መጠን ያለውን የኮንጎ ወንዝ ከአማዞን ቀጥሎ በዓለም ትልቅ የሚያደርገውና በሰኮንድ 4 ሺህ 700 ፍሰት መጠን ካለው የናይል ወንዝም በሁለተኝነት ደረጃ እንዲቀመጥ ያደርገዋል ብሏል፡፡

አስደማሚ ገጽታ ያለው የወንዙ ዱካ ከያዛቸው በርካታ ንጥረ-ነገሮች ባለፈ እስከ 800 ኪ. ሜትር የሚደርስ ቦታ መሸፈኑንም በማስታወቅ፡፡ የወንዙን ግዙፍነት በስፋት እንዳብራራው ከሆነ ዝቅ እያለ በሚሄድበት ጊዜ በከፍተኛ ሀይል የሚምዘገዘጉ ፏፏቴዎች ያሉት ሲሆን ግድቡም ስመ ጥሩ በሆነው በኢንጋ ፏፏቴ ላይ ይገኛል ብሏል አግድም በተዘረጉ በርካታ ፏፏቴዎች መካከል፡፡

4 ኪ.ሜትር ስፋት ያላቸው ዋና ዋና ፏፏቴዎች ቁልቁል 21.37 ሜትሮች ይወረወራል፡፡ ወደ መጠምዘዣ በኩል በርካታ መፋሰሻዎች፣ የውኃ ጅረቶችና ትናንሽ ደሴቶች መኖራቸውንም ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ እስከ 4 ሺህ 800 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይችላል፡፡ እስካሁን ድረስ ለኢንጋ 1 እና ኢንጋ 2 ፕሮጀክቶች የተጠለፈው የውሃ መጠን 30 በመቶ የሚደርስና ቀጣይ የሚገነባው ኢንጋ 3 ደግሞ የወንዙን ግማሽ ድረስ መጠቀም እንደሚችል ሲገለጽ ይህንን ሥራ ለማከናወን የገንዘብ መዋጮዎችንም የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ይሸፍናሉ ተብሏል፡፡ በመንግሥትና በህዝብ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ ነው የተባለው ታላቁ የኢንጋ 3 ግድብ ግንባታ በኢንዱስትሪ በበለጸጉና ቡድን-20 በተባሉ ሀገራት ዘንድም አድናቆት ካገኙ 10 ዋና ዋና ፕሮጀክቶች አንዱ ሆኖ ለልማት አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል ተብሏል፡፡

ገንዘቡ በመንግሥትና በህዝብ ትብብር የሚገኝ መሆኑን በማስታወቅ፡፡ ርካሽና ለተለያዩ ሥራዎች አመቺ የኃይል ምንጭ ከመሆን ባለፈ አህጉሪቱ አሁን ለተያያዘችበት የኢንዱስትሪ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የተባለለት ፕሮጀክት ለአካባቢው ሠላምና ለአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥርም አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገራችን ታላቁ ህዳሴ ግድብ አምሳያና አሠራር የተቀረጸው ይህ ከፍተኛ የኃይል ማመንጫ ግድብ ከጥቅሞቹ ባለፈ ሊያስከትል ይችላል የተባሉ ሥጋቶችም አሉት፡፡ ከባለ ድርሻ አካላት ብዛት የተነሳ ሊያስከትል የሚችለው ውዝግብ፣ የአካባቢ ብክለትና መራቆት፣ ከግዙፍነቱ አንጻር ሊፈጅ የሚችለው ጊዜ፣ ገንዘብና በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ጫናና እንዲሁም የሙስና ችግሮች ቅድሚያውን