የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ከማህበረሰቡ በመቀናጀት የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር ከፍተኛ ስራ መስራቱን ገለጸ
የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2017ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም መድረክ አካሂዷል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ለዊ እንደተናገሩት ከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጣን የሆነ ዕድገት እያሳች መሆኑን ተናግረዋል
በዚህም የከተማውን ዕድገት ተከትሎ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመከላከልና ያለውን ሠላምና ፀጥታ ይበልጥ ለማስጠበቅ የከተማው ፖሊስ ከፍተኛ ሚና ነበረው ብለዋል፡፡
በተለይ በከተማዋ የተጀመረውን የልማት ስራዎች ከዳር ማድረስ የሚቻለው በእጃችን ያለውን ሠላም ማስጠበቅ ስንችል ያሉት ከንቲባው ፖሊስ ማህበረሰቡን በማሳተፍ የጀመረውን አመርቂ ስራ በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ምናሉ ታደሰ እንደገለፁት በበጀት አመቱ ፖሊስ ከማህበረሰቡ በመቀናጀት የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር ከፍተኛ ስራ መስራቱን ተናግረዋል
በበጀት አመቱ በከተማዋ 344 የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የተፈፀሙ ሲሆን በባለፈው በጀት አመት ከነበረው አንፃር በ230 ወንጀሎች መቀነስ አሳይቷል ብለዋል።
የከተማው ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አስማረ ቶቲ በበኩላቸው የከተማው ህዝብ ለሠላሙ ከፀጥታ መዋቅር ጎን በመሰለፍ እያሳየ ያለው በጎ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በመድረኩ ላይ የከተማው አመራሮች የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል።
ዘጋቢ፡- ጦያር ይማም ከሚዛን ቅርንጫፍ

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ