ፖሊስ ከመደበኛ ስራዉ ጎን ለጎን ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ የሚያካሂደዉን የልማት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
ሀዋሳ፣ ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደውን ጨምሮ የማናጅመንት አካላት በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ ተገኝተው የማስ ስፖርት እንቅስቃሴና የአረንጋዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው እንደገለፁት ፖሊስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናው የተጠበቀ ንቁና ብቁ ዜጋ በመሆን ከሚያደርገው የወንጀልን መከላከልና የአከባቢው ሰላም ማስጠበቅ ስራው ባለፈ ከማህበረሰቡ ጋር የሚያደርገውን የልማት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል ።
የአሪ ዞን ፖሊስ የአከባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን የሚያደርገው የወንጀል መከላከል ስራው ባለፈ በአከባቢ ፅዳትና በሌሎች የልማት ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ብለው አሁንም የተካሄደውን የአረንጋዴ አሻራ ተከላ መርሃ ግብር በአግባቡ ፀድቆ ለአገልግሎት እንዲውል አስፈላጊውን እንክብካቤ መደረግ አለበት ብለዋል።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ በበኩላቸው ፖሊስም ሆነ ወጣቶች በስፖርት ጤንነታቸው ተጠብቆ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ በመገኘት ከዞኑ ማህበረሰብ ጋር በጋራ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ በማድረግ እንደ ሀገር በመትከል ማንሰራራት በሚል መርህ እየተካሄደ ባለው የአረንጋዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማካሄቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
የአሪ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር መሰለ ገብሬ ፖሊስ ከመደበኛዉ የወንጀል መከላከል ስራዉ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ጤና ለማስጠበቅ ፅዱ አከባቢን ለመፍጠር በተለያዩ አከባቢዎች የፅዳት ዘመቻ እያከናወነ መቆየመቱን ተናግረው በዛሬው እለትም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የማናጅመንት አካላት ጋር በመሆን በጂንካ ከተማ ዋና አደባባይ ላይ የማስ ስፖርትና እና በመምርያው ቅጥር ግቢ ውስጥ የተተከሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች እንዲፀድቁ በቀጣይ ከአባላቱ ጋር በመሆን አስፈላጊው እንክብካቤ ይደረጋል ብለዋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳነ በበኩላቸው የአሪ ዞን ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር የሚያደርጋቸው የወንጀል መከላከልም ሆነ የልማት ስራዎች የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማጠናከር ለሰላም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል ።
ዘጋቢ ፤- በናወርቅ መንግስቱ ከጂንካ ቅርንጫፍ

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ